Branaye lyrics

Songs   2024-06-26 11:21:15

Branaye lyrics

Loza:

የፀበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል፣

ተሸፍና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጥል፣

የት ነበር ያረግሁት ቀፎየን ስል ኖሬ፣

ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኖራ ማሬ።

ብራናዬ... አንች የልጅነቴ ጓዴ፣

ተረሣሽ ወይ የእሳት ዙሪያው ተረት ባንዴ፣

ብራናዬ... አንች የልጅነቴ ቀለም፣

እኔ እንዳንች ያጠናሁት ፊደል የለም።

ፍቅር የበዛባት ሠማሁ ከማንኩሣ፣

መንናለች ቢሉኝ ቢጫ ልብሥ ለብሣ፣

ሸዋ ከሩፋኤል ስጠብቃት ኖሬ፣

ንቤ ገዳም ገብታ ጎጃም ኖራ ማሬ፣

ሲኖዳ ዮሃንስ ያመት ጦሴን ይዤ፣

ጋማ ሽጦ ካሣ ሸኝቶኝ ከወንዜ፣

መጥቼ ከሸዋ ስጠብቃት ኖሬ፣

ለካ ገዳም ገብታ ጎጃም ኖራ ማሬ።(2)

ሀ ብለህ ተው ድገም ሲሉኝ ንሥሃ አባቴ፣

ዋ ብዬ ተማርሁኝ ወይ አለመስማቴ፣

ቀለም ወርቄ ቢሆን የቅርቤ ጓደኛ፣

ፍቅር ለያዘው ሠው ከልካይ የለው ዳኛ።

አሁን በማን ስቄ የልቤን ልካሠው፣

አንዴ በእሷ ፍቅር የተረታሁኝ ሠው፣

የት ርቄስ ባገኝ ከፍቅሯ መሸሻ፣

እሷ ሆና ለኔ ያለም መጨረሻ።

ማር ጧፍ ሆኜ...

ማር ጧፍ ሆና....

ማሬ ማሬ...ማሬ ማሬ...

ማሬ ማሬ...ማሬ ማሬ....

ኦሆሆሆ....

የፀበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል፣

ተሸፍና ዋርካ ከልሏት የዛፍ ጥል፣

የት ነበር ያረግሁት ቀፎየን ስል ኖሬ፣

ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኖራ ማሬ።

አ...አሃሃይ...

አ...አሃሃይ...

ብራናዬ... አንች የልጅነቴ ጓዴ፣

ተርሣሽ ወይ የእሣት ዙሪያው ተረት ባንዴ፣

ብራናዬ... አንች የልጅነቴ ቀለም፣

እኔ እንዳንች ያጠናሁት ፊደል የለም።

ላሳደገኝ ደብር የሥለት ልጅ ሆኜ፣

ካህን እንዴት ይፍታኝ ያንቺ እሥረኛ ሆኜ፣

በጊዜ ተደፋ የቀለሙ ቀንዴ፣

የኔ ፊደል መሆን ካንቺ አዳነኝ እንዴ።

ሣዋህድ ከኖርሁት ቅኔን ከደብተሬ፣

ተሽሎኝ ተገኜ ባላምባሩ ገብሬ።

ለካ ሠው አይድንም በደገመው መጽሓፍ፣

እንደሠም አቅልጦ ፍቅር ካረገው ጧፍ፣

ለካ ሠው አይድንም በኦሪቱ ገድል፣

ወንጌል ይዞ መጥቶ ፍቅር ካረገ ድል።

ማር ሲገባ ገዳም ድንጋይ ተንተርሶ፣

ጧፉም እንደመናኝ ህይወት ቢጫ ለብሶ፣

ወንጌል መነኮሱ በልጅነታቸው፣

ማር እስከጧፍ ሆኖ ዓለም ቢነዳቸው።

አንች የፍቅር ጥጌ ውድ ነሽ በጣሙን፣

መምጣቴ ነው በቃ እኔ አቃተኝ አሁን፣

አዲስ ዓለም ሆነ ባንቺ ሥል ወጋየሁ፣

እድሌ ሆነና ባጣሽ ተሠቃየሁ።

ማር ጧፍ ሆኜ...

ማር ጧፍ ሆና...

ማሬ ማሬ...

ጎጃም ኑራ ማሬ

ማሬ ማሬ...

ጎጃም ኑራ ማሬ

ኦሆሆ......

ማር ጧፍ ሆኖ... ገባ መቅደሥ፣

ነዶ ለኔ... ፀሎት ሊያደርሥ፣

ዲማ ጊዮርጊስ... ላይ ማንኩሣ፣

ያቺ ወንጌል... ቢጫ ለብሣ፣

ከንግዲማ... ቆብ አስጥዬ፣

እንዳልወስዳት... አባብዬ፣

ሠብልዬ ናት... እማሆዬ፣

ሠብልዬ ናት... እማሆዬ፣

ሠብላለም...

በቢጫው ቀለም፣

ሠብለኣዳም...

ገባሽ ወይ ገዳም፣

ወይ ገዳም....

ገባሽ ወይ ገዳም...

ኦሆሆሆ....ሆሆሆይይይ.....

See more
Teddy Afro more
  • country:Ethiopia
  • Languages:Amharic
  • Genre:Pop
  • Official site:http://www.teddyafromuzika.com
  • Wiki:https://en.wikipedia.org/wiki/Teddy_Afro
Teddy Afro Lyrics more
Excellent Songs recommendation
Popular Songs
Copyright 2023-2024 - www.lyricf.com All Rights Reserved